ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማምጣትና የህብረተሰቡን ችግር በላቀ ደረጃ ለመቅረፍ የሚያስችል አዉደ ምክክር ከዩኒቨርሲቲዉ መምህራን ጋር ተካሂደ፡፡

በምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕ/ጽ/ቤት ቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማምጣትና የህብረተሰቡን ችግር በላቀ ደረጃ ለመቅረፍ የሚያስችል አዉደ ምክክር ከዩኒቨርሲቲዉ መምህራን ጋር ተካሂደ፡፡በመምህራኑ የተዘጋጁ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለዉድድር ቀርበዉ ቀጣይ ለምሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ መለየታቸዉ ተጠቁሟል፡፡ዩኒቨርሲቲዉ ከመማር ማስተማር ስራዉ በተጨማሪ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን ሲያካህድ ቆይቷል፡፡ ተመራማሪዎች በምርምር ያገኙትን ተጨባጭ ግኝት በበጀት አስደግፈው ዘላቂ ለዉጥ እንድመጣ ከህብረተሰቡ ጋር በቁርኝት ሲሰራም ቆይቷል፡፡ማህበረሰቡ ችግሬ ነዉ ያላቸዉን ተግዳሮቶች በጥናትና ምርምር በመለየት ዩኒቨርሲቲው ባከናወናቸው መጠነ ሰፊ ስራዎች የማህበረሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጦች የጥናቱ ውጤቶች በተተገበሩባቸው አካባቢዎች ሊታዩ ችለዋል ፡፡

የዓለም መምህራን ቀን ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር በመተባበር "የመማር መብት ያለብቁ መምህራን አይታሰብም" በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲው በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

ዓለም አቀፉ የመምህራን ቀን እ.ኤ.አ ጥቅምት አምስት (october 5) በየአመቱ እንደሚከበር ነው ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የተገኘ መረጃ የሚያመላክተው፡፡የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባባር የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን

በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ገንደባ በድምቀት አክብሯል፡፡በበዓሉ ከሶስት መቶ የሚበልጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት ፣ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ መምህራን ማህበር አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የኢትዮጵያ

መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዩሃንስ በንቲ በዓሉ የመምህራንን የሥራ ሁኔታ ለማሻሻል እና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የተካሄደውን የትግል ሂደት ለመዘከር እ.ኤ.አ ከ1966ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የስኬት ሚስጢሩ በተሰማሩበት የሙያ መስክ ጠንክሮ መሥራት ነው-ፕሮፌሰር አሰፋ አስማረ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመምህራን ልማት ዘርፍ በተለይም የ0/70/30 ፖሊሲን ለማሳካት ዘረፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመማር ማስተማር ተግባር ላይ የሚሰማሩ ምሁራን ተለክቶ በሚሰጣቸው ተልዕኮች ማለትም በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ስራዎች እና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት እንዲሳተፉ ምቹ ምህዳር እንዲፈጠር ይሰራል፡፡ በተሳትፏቸው ልክና ባበረከቱት አስተዋጾ ውጤታቸው እየተመዘነ የደረጃ ዕድገት እንዲያገኙም ይደረጋል፡፡ በዚሁ መነሻ በ2009/10 ዓ.ም ዩኒቨርስቲው ለ84መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነት፣ለ8 መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት እና ለአንድ መምህር የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡ ማዕረጉ ከተሰጣቸው ምሁራን መካከል በዩኒቨርስቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከተሰጣቸው ከፕሮፌሰር አሰፋ አስማረ ጋር የዳሞታ መጽሔት በስራና በግል ሕይወታቸው ዙሪያ ቆይታ አድረጓል፡፡ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ ተመኝተናል፡፡

የአካል ጉዳተኝነት ሳይገድባቸው ራሳችውን የወገን ኩራት ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ገለጹ

ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞችን ቀን በተከበረበት ወቅት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ ታምራት በዩኒቨርሲቲው ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከማቅረብ ባለፈ ሁለንተናዊ አቅማቸውን ለማጎልበትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎች እየተሰሩ እንዳሉ የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተያያዥ ሌሎች ችግሮችንም ለመቅረፍ ደረጃ በደረጃ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ14.5 ሚሊየን ብር የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ (Dormitory) ገንብቶ አስረክቧል፡፡

ዩነቨርሲቲው በአከባቢው የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከማብቃት ረገድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የበርካታ ጎበዝ ተማሪዎች መፍለቂያ የሆነውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ በወላይታ ልማት ማህበር የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ በማሰብ ሁለት ህንፃዎችን ገንብቶ አስረክቧል፡፡

ትምህርት ቤቱ ባለፉት ጥቂት አመታት የተሻለ የትምህርት አቀባበል እያላቸው ወላጅ ያጡና የኢኮኖሚ አቅም በሌላቸው ተማሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ስሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን የተጀመረውን አበረታች ጅማሮ ለማስቀጠልና በትምህርት ቤቱ የሚስተዋለውን የተማሪዎች መኖሪያ ህንፃ እጥረት እንድቀርፍ በ14.5 ሚሊየን ብር ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል ሁለት ህንፃዎችን በመገንባትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

Pages

Subscribe to wolaita sodo University RSS

WSU MAP

Visitors

  • Total Visitors: 337003

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook