ዓለም አቀፉ የመምህራን ቀን እ.ኤ.አ ጥቅምት አምስት (october 5) በየአመቱ እንደሚከበር ነው ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የተገኘ መረጃ የሚያመላክተው፡፡የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባባር የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን
በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ገንደባ በድምቀት አክብሯል፡፡በበዓሉ ከሶስት መቶ የሚበልጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት ፣ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ መምህራን ማህበር አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የኢትዮጵያ
መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዩሃንስ በንቲ በዓሉ የመምህራንን የሥራ ሁኔታ ለማሻሻል እና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የተካሄደውን የትግል ሂደት ለመዘከር እ.ኤ.አ ከ1966ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡