Events Detail

img
img

የተመራማሪዎችን የምርምር አቅም ለማጎልበት እየተሰራ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ስነ-ዘዴዎችን በተመለከተ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡

Time: 5pm, Jan, 2018

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

በዩኒቨርሰቲው በመማር ማስተማር ስራ ላይ የተሰማሩ ከአንድ ሺህ አራት መቶ የሚበልጡ መምህራን ይገኛሉ፡፡ መምህራኑ ከመማር ማሰተማር ባለፈ የጥናትና ምርምር አቅማቸውን በመጠቀም የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ ይጠበቃል፡፡ ይህንኑን ለማጠናከር እንዲያስችል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንጋፋ ምሁራንን በመጋበዝ በምርምር ስነ ዘዴዎች ዙሪያ ለመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተሰጥቷል፡፡

በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ወንድሙ ወልዴ እንደገለፁት የጥናትና ምርምር ዘዴዎችን አስመልክቶ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ስልጠናው ወሳኝ እንደሆነ ተናገረዋል፡፡ ዶክተር ወንድሙ አክለውም፤ መምህራን ችግር ፈቺ በሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ የሚኖራቸው ተሳትፎ ጎልብቶ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በቅርቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለህትመት እንዲበቁ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን አመልክተዋል፡፡

በአለም ዓቀፍ ደረጃ በሚታተሙ ታዋቂና ተቀባይነት ባላቸው ጆርናሎች በማሳተም ረገድ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ የዩኒቨርሰቲው መምህራን ተሳትፏቸው እንዲጨምርና ተዓማኒነትና ተቀባይነት ያለው የምርምር ፅሁፍ እንዲዘጋጅ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ያለ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በዩኒቨርሰቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ታከለ ታደሰ በበኩላቸው በሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ በመመርኮዝ አካባቢያዊ ችግሮችን ከመቅረፍ ባለፈ፤ለሃገሪቱ ፈጣን ዕድገት አጋዥ የሚሆኑ ምርምሮች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠልና የትምህርትን ጥራት በማስጠበቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ የጋራ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ በጥናትና ምርምር ዘርፍ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችንና ስነ-ምግባራዊ ጥሰቶችን በማረም ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶክተር ታከለ ጠቁመዋል፡፡ ከምክክር መድረኩ ተሳታፊ መምህራን መካከል መምህር ግዛቸዉ ደሊሎ እና መምህርት ምህረት አብርሃም በበኩላቸዉ በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር መስክ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ስነ-ምግባራዊ ጥሰቶችን በማረም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታተሙ የጥናትና ምርምር የህትመት ውጤቶች ላይ ተሳተፏችን እንዲጎለብት ስልጠናው ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

More Events

ዩኒቨርሲቲው በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የህዝብ ፎረም አካሂዷል፡፡

Time: 7pm,1 March 2016

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

በፎረሙ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰንበቴ ቶማ ባደረጉት ንግግር ሆስፒታሉ ለተገልጋዮች እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም መልካም አስተዳደርን በቀጣይነት ለማስፈን ከማህብረሰቡ ጋር በመወያያትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መስተካከል በሚገባቸው ተግባራት ላይ ዩኒቨርሲቲው አፅንዖት ሰጥተው እንደሚያከናውን ገልጸዋል፡፡

Read More

̋በጥናትና ምርምር በመታገዝ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አኳያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያከናወናቸዉ ተግባራት አበረታች ናቸው˝ ሲሉ ባለድርሻ አካላት ተናገሩ፡፡

Time: 7pm,1 March 2016

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውናቸው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር አውደ-ጥናት አካሄደ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየ የምክክር አውደ-ጥናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አካሄደ፡፡

Read More