Events Detail

img
img

̋በጥናትና ምርምር በመታገዝ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አኳያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያከናወናቸዉ ተግባራት አበረታች ናቸው˝ ሲሉ ባለድርሻ አካላት ተናገሩ፡፡

Time: 5pm,june , 2015

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

̋በጥናትና ምርምር በመታገዝ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አኳያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያከናወናቸዉ ተግባራት አበረታች ናቸው˝ ሲሉ ባለድርሻ አካላት ተናገሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውናቸው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር አውደ-ጥናት አካሄደ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየ የምክክር አውደ-ጥናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አካሄደ፡፡ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብርሃም አላኖ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዩኒቨርሲቲው ያነገባቸውን ተልዕኮዎችን ማለትም የመማር ማስተማር ፣ የምርመርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትን በማቀኛጀት የትምህርት አግባብነትና ጥራትን ችግር ፈቺ ከሆኑ ምርምሮች ጋር በማቆራኘት በርካታ ተግባራትን እንዳከናወነና በቀጣይም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ አክለውም በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ-ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፁ ሲሆን ለሚያከናውናቸው ማህበረሰብ ተኮር ተግባራት የባለድርሻ አካላት አስተዋፅዖ የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ኩማ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የምርምር ሥራን በትኩረት እንዲሰራ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንደተከናወኑ እና በተለይም በ2008 ዓ/ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የአበላ ፋረቾ፣ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የኮካቴ እንዲሁም በዳውሮ ዞን የከጪ ምርምር ማዕከላትን በማቋቋም ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ተደራሽነቱን ከማስፋት አንፃር በቀጣይ ዓመታት ስነ-ምህዳርን መሠረት ያደረጉ ተጨማሪ የምርምር ማዕከላትን በማቋቋምና ተደራሽ በማድረግ መንግስት ያስቀመጠው በምግብ እህል ራስን የመቻል ዓላማ እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ዶ/ር ብርሃኑ አብራርተዋል ፡፡

በምክክር መድረኩ ዩኒቨርሲቲው ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም ያለውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡ በ2007 ዓ.ም በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ 56 የምርምር ስራዎች እና 21 ማህበረሰብ ተኮር አገልግሎቶች እንደተከናወኑ ተብራርቷል፡፡ በዘርፉ በሚቀጥሉት ጊዜያት ሊከናወኑ የተዘጋጁ የጥናትና ምርምር ፕሮፖዛሎች የቀረቡ ሲሆን በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዙሪያ ተመክሮበታል ፡፡

ውይይቱን ከተሳተፉ ባለድርሻ አካት መካከል አቶ አብርሃም ባቾሬ የወላይታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ በሰጡት አስተያየት በጥናትና ምርምር በመታገዝ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ዩኒቨርሲቲው አበረታች ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው በተለይም የማህበረሰቡን ባህል፣ ቋንቋና እሴትን ከማሳደግና በጥናትና ምርምር የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ የዩኒቨርሲቲውንም ሆነ የባለድርሻ አካለት ሚና ለመለየት አውደ-ጥናቱ አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ አበክረው ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይም የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ዘነበ በተላ የምክክር መድረኩ ዩኒቨርሲቲው ያከናወናቸውንና በቀጣይም የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር በማወቅ ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተጠናከረ መልኩ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ፋይዳዉ የጎላ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ በምክክር አውደ-ጥናቱ ላይ ከፌደራል፣ ከወላይታ እና ከዳውሮ ዞኖች ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ከአለም የምግብ ፕሮግራም /FAO/ እንዲሁም ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተጋበዙ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

More Events

ዩኒቨርሲቲው በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የህዝብ ፎረም አካሂዷል፡፡

Time: 7pm,1 March 2016

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

በፎረሙ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰንበቴ ቶማ ባደረጉት ንግግር ሆስፒታሉ ለተገልጋዮች እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም መልካም አስተዳደርን በቀጣይነት ለማስፈን ከማህብረሰቡ ጋር በመወያያትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መስተካከል በሚገባቸው ተግባራት ላይ ዩኒቨርሲቲው አፅንዖት ሰጥተው እንደሚያከናውን ገልጸዋል፡፡

Read More

̋በጥናትና ምርምር በመታገዝ የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አኳያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያከናወናቸዉ ተግባራት አበረታች ናቸው˝ ሲሉ ባለድርሻ አካላት ተናገሩ፡፡

Time: 7pm,1 March 2016

Location: Wolaita Sodo,Ethiopia

ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውናቸው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር አውደ-ጥናት አካሄደ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየ የምክክር አውደ-ጥናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አካሄደ፡፡

Read More