ዩኒቨርሲቲው በእንግዳ አቀባበልና ሆቴል አስተዳደር ትምህርት ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ ማስተማር ሊጀምር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በእንግዳ አቀባበልና ሆቴል አስተዳደር ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፤ ትምህርቱን ለመጀመር ባዘጋጀው የአውደ ምክክር ስነ-ሥርአት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተጋበዙ ምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ወንድሙ ወልዴ “የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥያቄ መነሻ በማድረግና በዘርፉ ያለውን ዕምቅ ሃብት በዕውቀት ለማስተዳደር ትምህርት ክፍሉን መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ይህም ማህበረሰቡ ከዘርፉ የሚያገኘውን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ከከተማ አስተዳደሩ በተሰጠ 20 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ለማስተማሪያ አገልግሎት ህንፃ የሚሆን ቦታ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ በማራ ጫሬ ቀበሌ ለማስገንባት የዲዛይን ስራዎችን መጠናቀቁንም አስታውቀዋል። እንደ ዶክተር ወንድሙ ገለጻ የማስተማሪያ ሆቴሉ ግንባታ በቀጣይ ሦስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ሥርአተ ትምህርቱ የአገር አቀፍ ስርዓተ ትምህርትና ፖሊሲን ግምት ውስጥ ከማስገባት ባለፈ አገራዊ ምላሽ እንዲሰጥ ተደርጎ መቀረጹን የተናገሩት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን አቶ ታርኩ ቆልቻ ናቸው፡፡ዩኒቨርሲቲው ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ በ2011 የትምህርት ዘመን ከ30 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በራሱ ግቢ ውስጥ ማስተማር እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡ተማሪዎችን በንድፈ ሃሳብና በተግባር ለማስተማር በአሁኑ ወቅት የመምህራን ቅጥርና አስፈላጊ ግብአቶች እየተሟሉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡በመድረኩ ከተሳታፉ ምሁራን መካከል ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እንግዳ አቀባበልና የሆቴል አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አማረ ነጋ እንደገለጹት እንደአገር በተለይም የደቡብ ክልል ዓለምን መሳብ የሚችልና ዕምቅ የሆነ የባህል ሃብት እያለው በተሻለ መጠቀም ያልተቻለው ዘርፉ በሳይንሳዊ መንገድ ባለመመራቱ ነው ብለዋል፡፡

WSU MAP

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook