የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ለማኔጅመንት ካውንስል አባላት እውቅና ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ለማኔጅመንት ካውንስል አባላት እውቅና ሰጠ (ወሶዩ፣ ኮጉዳ፣ ሰኔ 01/2012 ዓ.ም)
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባካሄደው የ2013 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተቋሙ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት (ደማቅ አረንጓዴ) እንዲያስመዘግብ ለተጉ የማኔጅመንት ካውንስል አባላት ምስጋናው ዕውቅና አበረከተ፡፡
**************
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባካሄደው የ2013 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 96.4% በማምጣት እጅግ በጣም ከፍተኛ (ደማቅ አረንጓዴ) ውጤት አስመዝግቧል።
ዩኒቨርሲቲው ይህን ውጤት ሊያገኝ የቻለው በ9 መመዘኛ መስፈርቶች በዋናነትም በሰላማዊ መማር ማስተማር፣ በሠለምና ደህንነት፣ ኮሮናን በመከላከል፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በዓባይ ግድብ ተሳትፎ፣ ለሥራ ምቹ አከባቢ ከመፍጠር ረገድ፣ በእቅድ አፈፃጸም፣ በተማሪዎች አገልግሎት እና በአመራር ድጋፍና ክትትል እንደሆነ ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም በትላንትናው ዕለት ተቋሙ ላስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም የማኔጅመንት ካውንስል አመራር አባላት ሚና ጉልህ በመሆኑ የምስጋና ዕውቅና መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለአመራሩ እውቅና ሰጥቷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ተቋሙ ከመደበኛ መማር ማስተማር፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ ከአሳታፊ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት ተግባር በተጨማሪ በየዘርፉ በሚከናወኑ ስራዎች የአገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ፤ ብልሹ አሰራርን በመከላከልና መልካም አስተዳደርን በማስፈን፤ ተቋምን በማዘመን፤ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ፈጣን፥ ቀልጣፋና ተገልጋይ ተኮር ተግባራትን በማከናወን የተገኘ ውጤት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት በትብብር መስራት ለተገኘው ውጤት ጉልህ ድርሻ እንደነበረውም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የማኔጅመንት ካውንስል አመራር አባላትም የተዘጋጀላቸውን የምስጋና ምስክር ዕውቅና ወረቀት ከማኔጅመነት አባላት እጅ ተቀብለዋል፡፡

Category: 

WSU MAP

Visitors

  • Total Visitors: 337317

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook