የዩኒቨርሲቲው ቲቺንግ እና ሪፌራል ሆስፒታል ላለፉት 90 ዓመታት ያልተቋረጠ የህክምና አገልገሎት ለህብረተሰቡ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሆስፒታሉ በዩኒቨርሲቲው መተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂና በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ ለወላይታና አጎራባች ዞኖች ማህበረሰብ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ሆስፒታሉ የኩላሊት እጥበት ህክምና ለመስጠት የሚያስችለውን ዘመናዊ ማሽን ከቅዱስ ጻውሎስ ሆስፒታል ጋር በተፈጠረ መልካም ግንኙነት ያገኘ ሲሆን፣ በቀን 8 ታካሚዎችን ማስተናገድ የሚስችል መሆኑ ተመልክቷል፡፡ህክምናው ከቀላል እስከ ከባድ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም ለህክምና የሚወጣውን ጊዜ፣ ጉልበትና ወጪ እንደሚቆጥብ ተገልጿል፡፡ የኩላሊት እጥበት ህክምና ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ሆስፒታሉ ሌሎች ተጓዳኝ የህክምና አገልግሎቶችን ጨምሮ የሪፈራል አገልግሎት ይሰጣል፡፡ሪፈራል ሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን አስመልክቶ ባዘጋጀው የህዝብ ፎረም አስተያየታቸውን የሰጡት ተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ ቢመጣም አገልግሎቱን ከታካሚው ቁጥርና ፍላጎት ጋር ለማጣጣም ገና ብዙ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
Category: