የቡና ምርታማነትንና ጥራትን በማሻሻል የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ዘርፉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

ዩኒቨረስቲው  የወላይታ ቡና ምርትና ምርታማነት፣ ጥራት፣ ግብይትና እሴት ማሻሻያን አስመልክቶ ከሰሞኑ አውደ ምክክር አካሂዷል፡፡

በዩኒቨረስቲው ግብርና ኮሌጅ አዘጋጅነት በተካሄደው አውደ ምክክር መድረክ ከወላይታ ዞን  12ቱም  ወረዳዎች  የተውጣጡ  የእርሻና  ተፈጥሮ  ሀብት  ባለሙያዎች፣    የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በዩኒቨረስቲው የግብርና ኮሌጅ ዲን ረ/ፕሮፌሰር አስራት ወርቁ በወላይታ ዞን የቡና ምርትና ምርታማነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ለቡና ምርትና ምርታማነት ማነቆ የሚሆኑ ተግዳሮቶችን በጥናትና ምርምር በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት በማስፈለጉ ይህ የምክክር  መድረክ መዘጋጀቱንም አውስተዋል፡፡

የቡና አመራረት ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ምርታማ የቡና ዝርያዎችን አለመጠቀምና በቴክኖሎጂ ያለመደገፍ ችግርን ለመቅረፍና በግብይት ላይ የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀ የስልጠና ምክክር መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ስነምህዳርን ታሳቢ በማድረግ በናን በስፔሻላይዜሽን ማምረት የሚችሉ የቦሎሶ ቦምቤ፣ዳሞት ጋሌና ሶዶ ዙሪያ ወረዳዎች ምርታማ የሚሆኑ የቡና ዝርያዎችን ለመትከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅ በዩኒቨርሲቲው መደረጉን አቶ አስራት ጠቁመዋል፡፡

አቶ አስራት አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከጅማና አዋዳ ምርምር ጣቢያዎች አዳዲስ የቡና ዝርያዎችን በማስመጣት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተጠቃሚነቱን በቅርበት ማረጋገጥ እንዲቻል የዘር ብዜትን የማስፋፋትና የማሰራጨት ስራን በስፋት ለማከናወን ማቀዱንም ሃላፊው አውስተዋል፡፡

በአውደ ምክክሩ የተገኙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌታሁን ጋረዳው በበኩላቸው  ዩኒቨረስቲው የአከባቢውን ስነ-ምህዳር ታሳቢ በማድረግ ችግር ፈች የሆኑ ምርምሮችን እየሰራ መቆየቱ የሚያስመስግን መሆኑን ጠቁመው የወላይታ ቡና ምርትና ምርታማነት ብሎም የግብይት እሴት ለማሻሻል እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም ዶ/ር ጌታሁን ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨረስቲው የሕዝቡን ፍላጎትና ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየሰራ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተናገሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቡና ምርትና ምርታማነትን በተመለከተ የወላይታ ቡና በራሱ ስም እስኪጠራ ድረስ ለመስራት እንደታቀደ አብራርተዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ተሳታፊና በወላይታ ዞን የገጠር ዘርፍ ፖሊቲካና አደረጃጀት ኃላፊ  የሆኑት አቶ ጥበቡ ዮሐንስ በበኩላቸው ከ1950ዎቹ ጀምሮ ወላይታ አከባቢ ለዓለም አቀፍ ገበያ ጭምር የቡና ምርት የሚያቀርብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች የቡና ምርትና ምርታማነት ተዳክሞ ከዓለም አቀፍም ሆነ ከአከባቢ ገበያ መጥፋቱንም አቶ ጥበቡ አስታውሰዋል፡፡

የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻል ያረጁ ቡናዎችን ነቅሎ አድስ በመትከል ብሎም ቡናን በዘመናዊና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሆነ መንገድ እንዲቀርብ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ርብርብ አስፈላጊ እንደሆነ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ጥራት ያለው ቡና እንዲመረት በማድረግ ቡናችን ታዋቂ እንዲሆንና የአርሶ አደሮቻችን ተጠቃሚነት እንድረጋገጥ ተረባርበን መስራት አለብን ሲሉም መልዕክታቸውን አቶ ጥበቡ አስተላልፈዋል፡፡

የወላይታ ቡና ምርትና ምርታማነት፤ጥራትና ግብይት ፕሮከጀክት ዋና አስተባባርና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨረስቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ሹምቡሎ በበኩላቸው የቡና ዝሪያዎች እንዳይጠፉ ስነ ምህዳርን መሰረት ባደረገ መልኩ አርሶ አደሩ ዝርያን የማዳቀል፤ችግኝ የማፍላት ስራን እስከ ድህረ ምርት ያለውን ሂደት በዕውቀት እንዲመራ ፕሮጀክቱ አጋዥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ጤናማ የቡና ግብይት ስርዓት ተፈጥሮ አርሶ አርሶ አደሩ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆንም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ፕሮጀክቱ የወላይታ ቡና የምርታማነት ችግርን ከመቅረፉም ባለፈ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት ጠቀመታው ጉልህ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡የምርታማነትን ፓኬጅን በጠበቀ መልኩ መስራት ከተቻለ የቡና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚቻልም አስገንዘበዋል፡፡የአውደ ምክክሩ ተሳታፊዎች በአከባቢው የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለቡና ጥራትና ግብይት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል በማለት የዘገበው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨረስቲ ኮሚዩኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኑኘት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

WSU MAP

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook