ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአገር እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እስካሁን ድረስ 81 ያህል ስምምት መፈራረም ተችሏል፡፡

 
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአገር እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘርፉን መልሶ በማደራጀት እና የጉድኝት አግባብን በማጠናከር እስካሁን ድረስ 81 ያህል ስምምት መፈራረም ተችሏል፡፡
 
------------------------------------------------------------------------
 
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተከናወኑ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራዎች በወፍ በረር ሲቃኝ፦
የውል ስምምነት አግባብ ሲታይ በሀገር ውስጥ /በሀገር አቀፍ ደረጃ 54 ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ግንኙነት መስክ የተፈረመ የስምምነት ብዛት 27 መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
በአገር እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መስክ ከተፈረሙ 81 የውል ስምምነቶች ውስጥ 15 ያህሉ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ ቀሪዎቹን ወደ ስራ ለማስገባት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ወደ ስራ ከገቡ 15 በጋራ የመስራት የጉድኝት እና ተግባቦት ተግባራት ከ95 ሚሊየን የሚበልጥ ሀበት የማሰባሰብና ሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥራ ተሰርቷል፡፡
በአገር እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፈ በጋራ ለመስራት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ለህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም በተቀናጀ መልኩ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ያሳውቃል፡፡
®
• እስካሁን ድረስ የተፈረሙ የሀገር እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ስምምነት ብዛት=  81
• በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈረመ ስምምነት ብዛት= 54
•  በዓለም አቀፍ ግንኙነት የተፈረሙ የስምምነት ብዛት= 27 
• ወደ ሥራ የገቡ የውል ስምምነቶች ብዛት=15
• ከነዚህ ግንኙነቶች የተገኘ የገንዘብ መጠን= 95, 355,958.00 birr

Category: 

WSU MAP

Visitors

  • Total Visitors: 337434

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook