ሃገርቱ የምትፈልገውን ብቁና ወሳኝ የሰው ኃይል ለማፍራትና በዘርፉ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን ይችላል የተባለለት የትምህርት ፍኖተ ካርታ ግባዓት ማሰባሰቢያ ላይ ትኩረት ያደረገው የምክክር መደረክ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱ ተገለፀ፡፡

wolaita sodo university

በምክክር  መደረኩ   ብቁ፣ተወዳዳሪና በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ማፍራት ለሃገር  ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ባለድረሻ አካላት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ መረባረብ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡ለአስራ ሁለት አመታት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ በምሁራን ተጠንቶና ተተችቶ የቀረበው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ግብአት ማሰባሰቢያ የምክክርመድረክ   "የኢትዮጵያ ትምህርትና ሥልጠና ጉዞ ከየት ወደየትና የፖሊሲ ትግበራ ችግሮች"     በሚል ርዕስ በዩኒቨርሲቲው ተካሂዷል፡፡    በአውደ ምክክሩ ከ 4ሺህ የሚበልጡ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ማነቆ በሆኑ ችግሮች እና በመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል፡፡በምክክር መደረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  የዩኒቨርሲቲው   ፕሬዝዳንት     / ሳሙኤል ኡርቃቶ     ትምህርት    የአገርን ሁለንተናዊ   እድገት ለማረጋገጥና   የዜጎችን  የኑሮ   ደራጃ ለማሻሻል     የማይተካ    ሚና   እንዳለው     ተናግረዋል፡፡

ብቃት ያለውን የሰው ኃይል ማፍራት የሚቻለው የትምህርትን ጥራት በማስጠበቅ መሆኑነን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ በትምህርቱ ሴክተር የሚስተዋሉ ውስንነትቶችን ለመቅረፍና መፍትሄ ለማበጀት ተብሎ የታቀደው የትምህርና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና በመሆኑ ባለ ድርሻ አካላት ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦችን በማፍለቅ ለዝግጅቱ መስመር የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል አክለውም ብቁ፣ተወዳዳሪና በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ማፍራት ለአንድ አገር ዘላቂ የልማት ግቦች እውን መሆንና ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ  በመሆኑ ቅንጅታዊ የአሰራር መርህዎን መከተል ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በፊት በትምህርቱ ሴክተር ሲስተዋሉ የነበሩና ለትምህርት ጥራት ማነቆ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች የተንፀባረቁበት ብሎም የትምህርት ስርዓቱን አንድ ደረጃ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ አቅጣጫዎች የተጠቆሙበት  መድረክ መሆኑን የተናገሩት የዩነቨርሲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳን ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ ናቸው ፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪም በአውደ ምክክሩ ተሳታፊዎችና ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመጠቆም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥና ዘላቂ ለውጥ አበክረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አውስተዋል፡፡
በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት መድረክ ተሳታፊ ከሆኑ መምህራን መካከል ዶ/ር እዮብ እሼቱ፣ መምህር አሸብር ጎግሌ እና መምህርት አብዮት ገብረ መድህን በአሁን ሰዓት አገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት የተቋቋሙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስርአተ ትምህርታቸው የዘመኑ ቴክኖሎጂ በሚፈቅደውና የተወዳዳሪነት መርህዎን መከተል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ተቋማቱ በስርአተ ትምህርታቸው የሚያካትቱትን መርሃ-ግብሮች ጭምር  ተግባራዊ ከማድረጋቸው በፊት በውይይት መድረኮች አዳብረውና የብዙሃኑ ፍላጎት የሆኑ ገዢ ሃሳቦችን አካተው ማጽደቃቸው በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት ሚናቸው ጉልህ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች አክለውም ባለፉት አመታት በትምህርቱ ዘርፍ መጠነ-ሰፊ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ ስርዓተ ትምህርቱን በማሻሻል ተማሪዎች ተገቢውን እውቀት በጥራት አግኝተው ውጤታማ እንዲሆኑ ከትግበራ በፊት እንዲህ ዓይነቱ በየመክክር መድረክ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

የትምህርትን ጥራት በዘላቂነት ለማስጠበቅ እንዲቻል በአውደ ምክክሩ የመምህራን ደመወዝና ጥቅማጥቅ መሻሻልና መከበር እንዳለበት፣የግል ትምህርት ተቋማት ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ፣የአካዳሚክ ነፃነት መጠበቅ መቻል እንዳለበት፣ እንዲሁም ተማሪዎችን በስነምግባርና በእውቀት በተገቢው ለመቅረፅ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሳታፊዎቹ አበክረው ጠቁመዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው አዘጋጅነት በተካሄደው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ የኢትዮጵያ የትምህርት እና ስልጠና ስርዓት፤የስልጠና ፖሊስ አመራርና አስተዳደር፤ፍኖተ ካርታ-ቴክንክና ሙያና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ችግሮች እና የመፍትሄ ሐሳቦች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደርጓል፡፡
በአውድ ምክክሩ የተቋሙ የ2010 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2011ዓ.ም መሪ ዕቅድ ቀርቦ መተቸቱንና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መቀመጡን የዘገበው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶረት ነው፡፡  

WSU MAP

CONNECT WITH US

We are on Social Networks. Follow us & get in touch.

The offitial address of the university:-

Twitter     @WSodoUniversity

Facebook